በዚህ ታሪካዊና በመስመር ላይ በሚካሄደው የእምነት መሪዎች ስብሰባ ላይ ይቀላቀሉን

ንዑስ ርዕስ፤ በሕይወታችን ዘመን ላይ ተላቁን ተልእኮ ለማፋጠን ራዕያችንን ይጋሩን

የካቲት 15-16, 2014 | |አየር ላይ ዝግጅት | 12 ቋንቋዎች

ኢየሱስ ከ2000 ያህል ዓመታት በፊት ታላቁን ተልእኮ ሰጠን፤

በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አሕዛብን ደቀ መዛሙርት ማድረግ። 2033 የታላቁ ተልእኮ 2000 ኛ ዓመት መታሰብያ ነው፣ እናም ሁሉም ሰው ፣  በየትኛውም ስፍራ መጽሐፍ ቅዱስን፣ አማኝን እና የክርስቶስን አካል ማግኘቱን ማረጋገጡ የኛ ድርሻ ነው።

FTT Accelerate ወደ ጠፉት እንዴት ብለን በአዲስ መንገድ መድረስ እንደምንችልና እንዴት ብለን አብረን መስራት እንደምንችልና እንዳለብን እንዲሁም የእኛ ትውልድ እንዴት ብሎ የታላቁ ተልእኮን የመፈፅም ሥራውን ማፈጠን እንዳለበት የሚያስችለንን ራዕይ በቅድሚያ መስማት የምንችልበት አስፈላጊ የሆነ ስብሰባ ነው። በመጭው የካቲት ወር ፣ ልክ እንደርስዎ ያሉትን ተደማጭነት ያላቸውን የቤተክርስቲያንና የድርጅት መሪዎችን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች እንዲሰባሰቡ፣ እንዲቀናጁና ለዚህ ራዕይ እንድያበረክቱ ጋብዘናል።

እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

-የማቴዎስ ወንጌል 28:19-20

መጋቢ ሪክ ዋረን እና ሌሎች ቁልፍ የሐሳብ መሪዎች አንዳያመልጡዎ

Rick Warren

መጋቢ ሪክ ዋረን

መጋቢ እና ዓለም አቀፋዊ ተፅእኖ ፈጣሪ ፥ የ Finishing the Task ዋና ዳይሬክተር ፥ የ Purpose Driven Life ደራሲ ፥ የ Saddleback ቤተክርስቲያን ፣ Purpose Driven Network ፣ the PEACE Plan እና Daily Hope መስራች።

ጆን ቼስናት

የ Wycliffe Illuminations Network ፕሬዚደንት እና የ Finishing the Task መፅሐፍ ቅዱስ ቅንጅት ኃላፊ

ሊዛ ፓክ

የ Finishing the Task ዓለማቀፋዊ እቅድ አውጪ

ጆሽ ነዌል

ዋና ዳይሬክተር ፥ ኢየሱስ ፊልም ፥ የወንጌላዊ ተነሳሽነቶች እና የ Finishing the Task አማኞች ቅንጅት ኃላፊ

በቀለ ሻንቆ

የ GCM ዓለማቀፋዊ የቤተክርስቲያን ተከላ መስራችና ፕሬዚደንት እንዲሁም የ Finishing the Task የክርስቶስ አካል ቅንጅት ኃላፊ

ጄሰን ሃበርድ

ዋና ዳይሬክተር ፥ ዓለማቀፍ የፅሎት ግንኙነት እና የ Finishing the Task የፅሎት ተግባር ቅንጅት ኃላፊ

Finishing the Task የሚኖረው መላው የክርስቶስን አካል ለማሰባሰብና ወደ ሁሉም ሰው ፣ በየትኛውም ስፍራ መጽሐፍ ቅዱስን፣ አማኝን እና የክርስቶስን አካል ማግኘቱን ወደ ማረጋገጥ ግቡ ለማፋጠን ነው።

FTT ACCELERATE ን ልታጡ የማትፈልጉበት ምክንያት

ታላቁን ተልእኮ እንፈፅም ዘንድ ለመስማማት በሚደረገው የዚህ ወሳኝ ስብሰባ አካል ይሁኑ

  • ወንጌል ስላልደረሳቸውና ስለ አላማችን ማለትም ፣ ሁሉም ሰው በየትኛውም ስፍራ መጽሐፍ ቅዱስን ፥ አማኝን እና የክርስቶስ አካልን ስለማግኝቱ በአንድነት ለመስራት ስላለንበት ሁኔታ አስቀድመው ከሚሰሙት መካከል ይሁኑ።
  • ስለ 2025 ግቦች ጋር እርስ በእርሳችሁ ለመስማማት ከዓለማቀፋዊ የቤተክርስቲያንና የተልዕኮ ድርጅት መሪዎች ጋር ይገናኙ።
  • በቁልፍ ተነሳሽነቶች ላይ አጋር ለመሆን ከሎሎች አለማቀፋዊ መሪዎች ጋር ይተባበሩና ያመልኩ።

የካቲት 15-16, 2014

ይታጠቁና ቃሉን ያሰራጩ!

Contribute to Finishing the Task

Help bring the transformational hope of Jesus to the places that need it most.